Ethiopian news and information update

ከዮሐንስ ታከለ

 ጨለማ ከፍቶ ባገራችን፣ ኮረንቲ ጠፍቶ ከተማችን

ማየት ቢያስጠላው፣ ቢያንገሸግሸው ውርደታችን

ሀገር ተጣማ ተጠናግራ፣ በጣር ተይዛ ስታጓራ

ማን ይሆን ጀግና የሚሰራ፣ ኢትዮጵያ ታማ ስትጣራ

አለሁልሽ አላት ሀይለ መድህን አበራ፡፡

ችቦውን ለኩሦ

አየር ላየር ተመዘግዝጎ

አስተጋባ ብሶቷን

ፍልጠት ቁርጠቷን

የኢትዮጵያን ሠራ ሥራ

የበላይ የልጅ ልጅ፣ ሀይለ መድህን አበራ

ለጣሊያን ወረራ፣ እንቆቆ እንደሆነው

የበላይ ዘለቀ፣ ሁሌ እንደምንጠራዉ

ሀይለ መድህን፣ ለጋው ጋሻውን አነሳው

ጣሊያኑን አባሮ፣ አየሩን አስነሳው

አጨሰው ለኮሰው፣ እያቀጣጠለው፡፡

በምድር በሰማይ

ኢትዮጵያን የሚያሳይ

ትልቅ ሥራ ሠራ፣ ምን ሁን ወያኔ ፣

የባንዳ ምስለኔ፣ የሀገር ፍቅረ ጠኔ

አበደ ይሉታል የታለ ያበደው

ጀግና ችን ቢወጣ፣ ከድፍን አገር ሰው፡፡

Leave a comment